DID U KNOW️⁉️ 头像

消息来源频道

DID U KNOW️⁉️

@diduknow0

频道37,190 位成员公开可见持续更新

⭐️IF YOU DON'T KNOW NOW YOU KNOW ✅Strange & Amazing & Facts ✅Technology Facts ✅World Records ✅Life Hacks Buy Ads: https://telega.io/c/diduknow0 https://adsly.me/@diduknow0 Contact us ✳️via bot @diduknow011

成员规模37,190 位成员
在线情况待同步
消息总数15,495 条消息
浏览量总数0 次浏览

在这个频道里搜索消息……

t.me/diduknow0

👩🏽‍🦰👱🏽‍♀️የፀጉር መርገፍ👱🏽‍♀️👩🏽‍🦰
የፀጉር መርገፍ በጭንቅላታችን ላይ ያለን ፀጉር ብቻ ሳይሆን ሌላ አካላቶቻችን ላይ ያለን ፀጉር ያጠቃልላል፡፡
ለዛሬ የፀጉር መርገፍ መንስኤዎችን እና የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ምን ማድረግ እንዳለብን እንነጋገራለን፡፡
መንስኤዎች ምንድን ናቸው?
👉🏾 በዘር፡- ወንዶች ላይ የፀጉር መሸሽ እና መመለጥ፤ ሴቶች ላይ ደግሞ የፀጉር መሸሽ እና መሳሳት
👉🏾 ሰውነታችንን በሚያጠቁ በሽታዎች፡- የታይሮይድ ህመሞች፣ የካንሰር ህመሞች
👉🏾 መድሃኒቶች፡- የካንሰር ህክምናዎች
እጅግ በጣም የሚያጠብቅ ሹሩባ
👉🏾 የአእምሮ ጭንቀት
👉🏾 ለፀጉር እድገት የምንጠቀማቸው ግብአቶች
ስለመንስዔው ማወቅ የፀጉር መርገፍን እንዴት መከላከል እንዳለብን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል፡፡
🗒 ፀጉራችን ከመርገፉ በፊት የምናያቸው ምልክቶች...🗒
-የፀጉር መሳሳት
-በአንዳንድ የፀጉራችን ክፍል ውስጥ ባዶ የሆኑ ቦታዎች መኖር
-ፀጉራችንን በምናበጥርበት ወይም በምንታጠብበት ጊዜ የሚታይ የፀጉር መርገፍ
የፀጉር መርገፍን ለመከላከል ወይንም ለመቀነስ ማድረግ ያሉብን ነገሮች
-ለፀጉር የምንጠቀማቸው ግብአቶች ከተፈጥሮ የተሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ
-ሹሩባ በምንሰራበት ወቅት ላላ አድርጎ መሰራት
-ጭንቀታችንን ለቅርብ ለምንለው ሰው ማውራት
-በበሽታዎችና በመድሃኒቶች የሚመጡ የፀጉር መርገፎችን ከሃኪማችን ጋር በመነጋገር ማስተካከያዎችን ማድረግ
-እንደ ፊታችን ሁሉ ፀጉራችንንም መንከባከብ
ፀጉራችንን እንዴት መንከባከብ ይኖርብናል?
👉🏾ማንኛውም ነገር ለማደግ ግብአት እንደሚያስፈልገው ሁሉ ለፀጉርም ግብአት ያስፈልጋል፡፡ ፀጉራችንን በንፅህና መያዝ አስፈላጊ ነው፡፡ የሚመቸንን ሻምፖ እና ኮንዲሽነር በመሞከር ፀጉራችን ላይ የሚመጣውን ለውጥ ማስተዋል፤ የምንጠቀማቸው ግብአቶች ሰልፌት የሌላቸው መሆኑን በእቃው ላይ የሚፃፈውን ንጥረ ነገር ማየት ይኖርብናል፡፡
👉🏾ለፀጉራችን የሚስማማንን ቅባት መለየት፤ ፀጉር ከሰው ሰው ስለሚለይ እኛም ለፀጉራችንን የሚስማማንን ፀጉር በምናየው ለውጥ መወሰን ይኖርብናል፡፡
ለፀጉራችን ቢያንስ በ2 ሳምንት አንድ ጊዜ የተለየ እንክብካቤ ማድረግ ማለትም አቮካዶ፣ እርጎ፣ ቅቤን ፀጉር ላይ በመቀባት መንከባከብ ይኖርብናል።