ይድረስ👉 ለማይደርስልን መንግስት 😒
እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
እየተሰበርን ሰበር በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
እግረ መንገዳችን ፣ድንገት ከሞት ተርፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በተድላ
እንደምን ነህልን?
እንደምን ነህልን ካልንህስ በኋላ ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን፣ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር፣እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"መግደል መሸነፍ ነው"፣በሚል ፍልስፍና !
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ፣የብዙዎች ምርጫ
ፍትህ ለሚጠይቅ ፣ምትሰጥ መግለጫ
የእልፎች አሻጋሪ ፣የእልፎች እንቅፋት
ትኩረት የምትሰጥ
ከሰዎች ነፍስ ይልቅ ፣ለአበቦች መጥፋት
እንደምን ነህ አንተ?!
@best_profile_picss
እንደምነህ መንግስት እኛ አለን በደህና
ባመቻቸህልን የለውጥ ጎዳና
ሺዎችን ገብረን ፣ ለአንድ ብልፅግና
እየተሰበርን ሰበር በሚል ዜና
ተራ እየጠበቅን ፣ ለሞት ተሰልፈን
እግረ መንገዳችን ፣ድንገት ከሞት ተርፈን
ከደብዳቢ ጋራ
ደብዳቤ እስክንልክ፣በደማችን ፅፈን
እኛ አለን በተድላ
እንደምን ነህልን?
እንደምን ነህልን ካልንህስ በኋላ ?!
እኛ አለን በድሎት
እኛ አለን በፀሎት
ከገዳያችን ጋር ቀብር ስናስፈጥም
ስንኖር ኢትዮጵያዊ
ስንሞት ምን እንደሆንን፣ባናረጋግጥም
እኛ አለን በተአምር፣እኛ አለን በደህና
እየተገደልን
"መግደል መሸነፍ ነው"፣በሚል ፍልስፍና !
አንተ ግን እንዴት ነህ?
እልፎች ሚቃወሙህ፣የብዙዎች ምርጫ
ፍትህ ለሚጠይቅ ፣ምትሰጥ መግለጫ
የእልፎች አሻጋሪ ፣የእልፎች እንቅፋት
ትኩረት የምትሰጥ
ከሰዎች ነፍስ ይልቅ ፣ለአበቦች መጥፋት
እንደምን ነህ አንተ?!
@best_profile_picss